ኤርትራ፣ ሠራዊቷን ክተት እንዳላወጀችና በኢትዮጵያ ላይ “የወታደራዊ ትንኮሳ ድርጊቶችን” እንዳልፈጸመች በመግለጽ አሜሪካ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ባወጣችው መግለጫ አስተባብላለች።
ይልቁንም በቀጠናው ውጥረት ያሰፈነው፣ ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲ” ወይም “በወታደራዊ ኃይል” ወደብ ማግኘት አለብኝ በማለት የከፈተችው ዘመቻ ነው በማለት ኤርትራ መክሰሷን ዋዜማ ዘግባለች፡፡
ኤርትራ ይህን ያለችው፣ የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ላካሄደው የስሚ መድረክ በሰጠችው ምላሽ ነው።
ቋሚ ኮሚቴው በኤርትራ ላይ “ያልተረጋገጡ” ውንጀላዎችን አቅርቧል በማለት የከሰሰው የኤርትራ መግለጫ፣ ለቋሚ ኮሚቴው አስረጅ ኾነው የቀረቡ ባለሙያዎች ለውጥረቱ ምንጩ ‘የኤርትራ ወታደሮች የትግራይ ግዛቶችን ተቆጣጥረው መቀጠላቸው’ ነው ማለታቸውን አጣጥሏል።
ሴናተር ክሪስ ቫን ሆለን በመድረኩ ላይ፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት “ሊፈነዳ ተቃርቧል” በማለት መናገራቸውን ኤርትራ ጠቅሳለች።
ዋዜማ
