በኢትዮጵያ 5.1 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል

Date:



እሁድ መጋቢት 7 2017 ዓ.ም ከምሽት 3፡53 ላይ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት እነደነበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዝክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተመራማሪው ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ለኢቢሲ ዶትስትሪም ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይስተዋልበት በነበረው የፈንታሌ እና ዶፈን ተራራዎች መካከል ከሳቡሬ መንደር በስተምስራቅ በኩል ቀረብ ባለ ቦታ ላይ የተከሰተ ርዕደ መሬት መሆኑንም ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ለ9 ሰከንድ በቆየው ርዕደ መሬት አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ላይ ንዝረቱ ስለመሰማቱም ነው የገለጹልን።

በኢትዮጵያ ከአዋሽ በስተሰሜን 50 ኪ.ሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.1 መሆኑን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከመሬት በ10 ኪ.ሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ስለመፈጠሩም ይሄው ተቋም ያወጣው መረጃ ያመላክታል።

የርዕደ መሬቱ ንዝረት አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች ላይ ተሰምቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...