በከተማው ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ መታወቂያ ተሰርዟል

Date:

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የቀበሌ መታወቂያ እንዳይሰጥና እንዲሰረዝ እንዲሁም በከተማው ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጠው በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ብቻ መሆኑን አስታውቋል።

‎ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም ሰው በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ብቻ እንዲጠቀምና በከተማው በሁሉም ቀበሌያት መደበኛ መታወቂያ እንዳይሰጥና እንዲሰረዝ ነው አስተዳደር ምክር ቤቱ የወሰነው።

ከተማ አስተዳደሩ በከተማው የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ተግባራትና ወንጀሎች ለመከላከል በማሰብ ለማንኛውም ዓይነት አገልግሎቶች ህብረተሰቡ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ብቻ እንዲጠቀም አሳስቧል።

‎በከተማው ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ መታወቂያ እንደማይሰጥና እንደተሰረዘ ነው የተገለጸው።

ነዋሪዎች እንዲሁም በከተማው የሚንቀሳቀሱ ማንኛውም ግለሰብ ከዚህ በኃላ ምንም ዓይነት የቀበሌ መታወቂያ መጠቀም እንደማይቻልም አጽንኦት ሰጥቶ ገልጿል።

‎በመሆኑም የመደበኛ መታወቂያ የሰጠ እንዲሁም በመታወቂያው የተጠቀመ ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅም ነው ያሳሰበው።

መረጃው የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...