የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በሚሸጡ ትናንሽ ሱቆች ውስጥ እንጀራና ዳቦ መሸጥ መከልከሉን አስታውቋል፡፡
ክልከላው ከጤና አኳያ፣ የምግብነት ይዘት የሌላቸው አልፎ አልፎም መርዛማነት ይዘት ያላቸው እንደ አይጥ መርዝ፣ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች እና ሌሎችም ግብዓቶችን ለምግብነት ከሚውሉ ምርቶች ጋር መሸጥ ለጤና ጠንቅ በመሆናቸው ነው ክልከላው የሚደረገው ተብሏል፡፡
ነገር ግን እንጀራ እና ዳቦ በተፈቀደላቸው ስፍራዎች ለብቻው ለይቶ የሚሸጥ አካል ካለ ፍቃድ እንደሚያገኝ ተገልፆል፡፡አሁን ላይ በከተማው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተሰራ ሲሆን እንዲያስተካክሉ የሚደረግ ሲሆን ከቀጣይ ታህሳስ ወር ጀምሮ ግን እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ የባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ተናግረዋል።
በተጨማሪም እንጀራ እና ዳቦ የሚጓጓዝበትን ሂደት በጋሪ እና አግባብነት በሌለው መልኩ በመሆኑ በቀጣይ የቁጥጥር ስራዎች ይከናወናል ተብሏል፡፡
የህብረተሰቡን ጤና ጉዳት ላይ የሚጥሉ የተለያዩ ለተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ በመሆኑ ክልከላውን ተላልፈው የሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ እና ክልከላውን የተላለፉ ሱቆች ሲያጋጥሙ ለባለስልጣኑ በ8864 ጥቆማ መስጠት አለባቸው ሲሉ አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ተናግረዋል።
