በኬንያ የተጋለጠው የህፃናት የወሲብ ንግድ

Date:

ማሂ ማሂዩ ከኬንያ ዋና ከተማ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ኬንያን ዋነኛ የትራንስፖርት ማዕከል የሆነችው ከተማ አሁን አሁን በህፃናት የወሲብ ንግድ ታዋቂ ሆናለች።

በዚህች ከተማ ‘ማዳም’ ተብለው የሚታወቁ ሴቶች ዕድሜያቸው 13 አመት ጀምሮ የሆኑ ህጻናትን በወሲብ ንግድ ውስጥ ይሳተፋሉ።

ቢቢሲ በሰራው የምርመራ ዘገባ ይህንን አጋልጧል።

ኬንያ በግለሰቡ ፈቃድ ለገንዘብ የሚደረግን ወሲብ የሚከለክል ህግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የላትም ሆኖም ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን መነገድ ግን ከ10 አመት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት ያስቀጣል።

በዚህ ተግባር የተሰማራች ሴት ህጻናቱ ኮንዶም ይጠቀሙ እንደሆን ጥያቄ ቀርቦላት አንዳንዶቹ የበለጠ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ እንደማይጠቀሙና አንዳንዶቹ  ተገደው እንደማይጠቀሙ ገልፃለች። ህፃናቱም ከብዙ ሰዎች ጋር በአንድ ቀን የወሲብ ግንኙነት እንደሚፈጽሙም ነው የተናገረችው።

በአሁኑ ወቅት በኬንያ በወሲብ ንግድ ተገደው የሚሰሩ ህፃናት ቁጥር በውል አይታወቅም፤ ሆኖም በየቀኑ 30,000 ህጻናት በወሲብ ኢንዱስትሪ ውስጥ ይበዘበዛሉ ተብሎ ይገመታል።

ሌላኛው በዚህ ንግድ የተሰማራች ሴት ህፃናቱን ለወሲብ በመሸጥ በቂ ገቢ እያገኘች እንደሆነ ስትናገር በምርመራ ዘገባው ላይ ባለው ቅጂ ትደመጣለች።

ሴትየዋ በዚህ ንግድ መሰማራት ህገወጥ መሆኑን ጠቅሳ በድብቅ እና በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚሰራ በመግለጽ፥ ማንም ሰው ገንዘብ ከከፈለ ህጻናቱን ማግኘት እንደሚችል ነው የገለጸችው።

አክላም፥ በወሲብ ንግዱ ከ13 ዓመት ጀምሮ ያለች ህፃን እንዳሉና ለእያንዳንዱ ሴት 3000 ሽልንግ እንደምታስከፍል እና ከዛ ውስጥ 2500 ሸልንጉን ለራሷ እንደምትወስድ ትናገራለች።

ከህፃናቱ መካከል አንዷ በቀን በአማካይ ከ5 ወንዶች ጋር የወሲብ ግንኙነት እንደምታደርግም ተናግራለች።

ልጅቷ ቤተሰብ እንደሌላት ገልፃ ያለኮንዶም አላደርግም ብትል ከስራው ውጪ እንደምትሆን እና የምትሄድበት ቦታ እንደሌለ ስታስረዳ ነው በዘገባው የሚደመጠው።

በዚህ ኢንዱስትሪ ለ40 ዓመታት መቆየቷን የገለጸች አንዲት የ61 ዓመት ሴት አብዛኞቹ ሴቶች ወደዚህ ስራ የገቡት በቤተሰቦቻቸው ሲበደሉ እና እንክብካቤ ሲያጡ እንደሆነ ትናገራለች።

ሚሼል የተባለች ታዳጊ በ12 አመቷ ወደ ወሲብ ንግዱ በአንዲት ሴተ አማካኝነት እንደገባች ገልፃለች።

ሊሊያን የተባለች ሌላኛዋ የ19 ዓመት ሴት 12 ዓመት ሳለች ቤተሰቦቿን ካጣች በኋላ አጎቷ ገላዋን ስትታጠብ ቀርጿት ምስሉን ለጓደኞቿ እንደሸጠ እና ቀስ በቀስ ይደፍራት እንደነበር ተናግራለች።

ከእሱ ካመለጠች በኋላ በመኪና ሹፌር ተደፍራ ወደ ማሂ ማሂዩ ተወስዳ ወደ ወሲብ ንግድ መግባቷን ነው ያስረዳችው።

ይህች ከተማም በኬንያ ከፍተኛ የኤች አይቪ ኤድስ ተጋላጭነት ያየለባት ከተማ ነች ተብሏል።

‘ቤቢ ገርል’ የተባለ ድርጅት ማህበረሰቡን እያስተማረ እና ኮንዶምም እየሰጠ ቢገኝም ድርጅቱ ከመስከረም ጀምሮ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ በመነገሩ ለሴቶቹ ጭንቀትን ፈጥሯል።

እንደ ሊሊያን ያሉ ሴቶች በድርጅቱ እርዳታ ከዚህ ነገር ወጥተው የፎቶግራፍ ሙያ እየተማረች ትገኛለች።

እሷ ስትናገርም ምንም የምፈራው ነገር የለም ብላ ‘ቤቢ ገርል’ ያለፍኩበትን እንድረሳ አድርጎኛል ስትል የድርጅቱ አገልግሎት ማቆም ግን ብዙ እያገገሙ ያሉ ሴቶችን ስጋት ውስጥ ከቷል ስትል ስጋቷን ገልጻለች።

ቢቢሲ የቀረፃቸውን ማስረጃዎች ለኬንያ ፖሊስ ባለፈው መጋቢት ማስረከቡን ቢገልፅም ማንም የተያዘ ሰው የለም ተብሏል። በተጨማሪ በዘገባው የተካቱት ሰዎችም ከዛ በኋላ ቦታቸውን ቀይረዋል።

Source: BBC News Africa

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ነገ መደበኛ ስብሰባዉን እንደሚያካሂድ ገለጸ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት...

ትራምፕ የቲክ ቶክ ስምምነት ከቻይናው መሪ ዢ ጋር በሚኖራቸው ስብሰባ ሊጠናቀቅ ይችላል አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሳምንቱ መጨረሻ ከቻይና ፕሬዝዳንት...

የፊፋ የ2025 የአመቱ ምርጥ 26 እጩ ተጨዋቾች ይፋ ተደርጉ

ከሪያል ማድሪድ አምስት ተጨዋቾች ሲመረጡ ከባርሴሎና አራት ተጨዋቾች እጩ...

ቅዱስ ሲኖዶስ ለትግራይ አባቶች፣ ካህናትና ምዕመናን የሰላም ጥሪ አቀረበ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ...