ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ነገ መደበኛ ስብሰባዉን እንደሚያካሂድ ገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ ጥቅምት 18 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ይካሂዳል፡፡

በዚህ መደበኛ ስብሰባ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ለኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዕለቱ በሚካሄደው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ከምክር ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...