ትራምፕ የቲክ ቶክ ስምምነት ከቻይናው መሪ ዢ ጋር በሚኖራቸው ስብሰባ ሊጠናቀቅ ይችላል አሉ

Date:

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሳምንቱ መጨረሻ ከቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ቲክ ቶክ በአሜሪካ ባለው ቀጣይነት ዙሪያ ከቻይና ጋር የባለቤትነት መብት በተመለከተ ስምምነቱ ሊጠናቀቅ ይችላል ብለዋል ።

ትራምፕ በእስያ ጉብኝታቸው ከማሌዢያ ወደ ጃፓን ሲጓዙ “እኛ የምንወያይበት አንዱ ነገር ይህ ይሆናል” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የመጨረሻውን ስምምነት ለመፈረም እቅድ እንዳለቸው ተጠይቀው ነበር።

ትራምፕ ሲመልሱ “ከፕሬዚዳንት ዢ ይፋዊ ይሁንታ” ማግኘታቸውን እና ተጨማሪ ማረጋገጫ እንደሚጠብቁ በመግለፅ “ተጣዮቹ ሁለት ቀናት መጠበቅ” እንደሚመርጡ ተናግረዋል ። ትራምፕ “በጣም ጥሩ ንግግር እናደርጋለን እናም ለሁለቱም ሀገራት የተሳካ ግብይት እናካሂዳለን” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት ት በቲክ ቶክ ላይ የሚደረሰው ስምምነት ከቻይና ጋር በተደረገ ውይይት ሲሆን “ሁለቱ መሪዎች የፊታችን ሐሙስ እለት በደቡብ ኮሪያ ውስጥ ያንን ግብይት እንዲፈጽሙ” ይጠበቃል ብለዋል ።

ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ ከሚካሄደው የእስያ-ፓሲፊክ ኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ጉባኤ ጎን ለጎን ሐሙስ እለት ከቻይና አችልቸው ከዢ ጂፒንግ ጋር ይገናኛሉ። ሁለቱ በታሪፍ፣ ንግድ፣ ፌንታኒል፣ የአሜሪካ የግብርና ምርቶች እና ብርቅዬ የምድር ማዕድናት ጉዳይ ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትራምፕ በሴፕቴምበር ወር ላይ ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ በአዲስ የኮርፖሬት መዋቅር ከአሜሪካ ባለሀብቶች ጋር እንዲሠራ አስችሎታል በማለት ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ተፈራርመዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመተግበሪያው ላይ እገዳው በጥር 20 ተግባራዊ ሆኖ ነበር።ነገር ግን የትራምይ አስተዳደር የባለቤትነት መብትን ለማስተላለፍ በመሞከር ለአራት ጊዜ እገዳው ተራዝሟል።
ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...