በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የተገነባው ማዕከል እስካሁን ስራ አልጀመረም

Date:

የኢንጂነር ታደለ ብጡል የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

ኢንጂነር ታደለ ብጡል የባንክ ባለሙያ፣ ሲቪል መሀንዲስ እና ደራሲ ሲኾኑ፣ ማራዥት እና ሦስትዮሽ የተሰኙ የግጥም መድብሎች እንዲሁም የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፣ የሀኪም ወርቅነህ እሸቴ፣ የአፄ ቴዎድሮስ እና የልዑል አለማሁ ቴዎድሮስን ግለ ታሪኮች ፅፈዋል። የአማርኛ የምልክት ቋንቋ መዝገበ ቃላትንም አዘጋጅተዋል። ደራሲ እና ኢንጂነር ታደለ ብጡል በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ በመሳተፍም ይታወቃሉ። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የማታ ትምህርት ያስጀመሩ ናቸው። በታዋቂው አርበኛ የተሰየመውን ወንዲራድ ት/ቤትን ከሌሎች ጋር በመሆን አቋቁመዋል። የአክሱም ሀውልት ብሄራዊ አስመላሽ ኮሚቴ አባልም ነበሩ። የተለያዩ ባህላዊ እና ትውፊታዊ ቅርሶችን ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት በራሳቸው ወጪ ገዝተው በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ ሙዚየሞች በመለገስ ታሪካዊ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የ2008 ዓ.ም የበጎ ሰው ተሸላሚው የሀገር ባለውለታ ኢንጅነር ታደለ ብጡል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በ97 ዓመታቸው ነሐሴ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉ ሲኾን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም፣ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

‹‹ከለቻ›› መጽሐፍ እሁድ ይመረቃል

በጋዜጠኛ ሐብታሙ ባንታየሁ ‹‹ከለቻ›› በሚል ርዕስ የተጻፈ አዲስ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ጳጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል። ‹‹ከለቻ›› መጽሐፍ በዘውግ በኩል ረጅም ልቦለድ ሲሆን በ5 ምዕራፎች ተከፍሎ፣ በ96 ተቀንብቦ በ200 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል። በዚህ መጽሐፍ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይ ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ደራሲ ጌታቸው በለጠ እና ሌሎችም ሐሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የተገነባው ማዕከል እስካሁን ስራ አልጀመረም

ለዓመታት በግንባታ መጓተት ምክንያት ቆይቶ የነበረው ‹‹አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል›› ተመርቆ ለስራ ዝግጁ ከሆነ ወራት ቢያስቆጥርም አሁንም ስራ አለመጀመሩን ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል። አዳራሹ ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም ስለሚያስፈልገው መጓተቱን ያስታወቁት ፒያኒስትና በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የአሸናፊ ከበደ ሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ግርማ ይፍራሸዋ ናቸው። በአዳራሹ የሚገጠመው ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም ከውጭ ሀገር የሚገባ በመሆኑና እስካሁን ባለው ሂደት ገብቶ ባለመጠናቀቁ አዳራሹ ስራ ሳይጀምር መቆየቱን አቶ ግርማ ይፍራሸዋ ተናግረዋል። ከውጭ የሚመጡትን እቃዎች ከመጠበቅ ውጭ አዳራሹ ለስራ ምቹና ብቁ ነው በማለት ከመጪው መስከረም ወር  በፊት እንዲጠናቀቁ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ግርማ አክለው ገልጸዋል ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን...

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በሀገር-በቀል አቅም ለማጠናከር የሚያስችል ግብረ ኃይል ተቋቋመ

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሀገር ውስጥ አቅም ላይ...

ዶናልድ ትራምፕ የ’ICE’ ተቋምን ስም ወደ ‘NICE’ ለመቀየር መወሰናቸው አነጋጋሪ ሆነ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገሪቱ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ አስከባሪ...

የአዲስ አፍሪካ ሪል እስቴት ኤክስፖ የአራት ቀናት ስኬታማ የሥራ ክንውን

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት አልሚዎች ማኅበር ባለቤትነት እንዲሁም በከተማ መሠረተ...