በዱባይ ወንጀል ፈጽመው በኢትዮጵያ ተደብቀዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች!!

Date:

በዱባይ ወንጀል ሠርተው በኢትዮጵያ የተሸሸጉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እየተካሄደ  መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል አስታወቁ።

ኮሚሽነሩ ይህንን ያስታወቁት፤ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የዱባይ ፖሊስ የምርመራ ቡድን ጋር በወንጀል ምርመራ ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው።

በዱባይ ወንጀል ሠርተው በኢትዮጵያ ተሸሸገው የነበሩና በቁጥጥር ስር ውለው ምርምራ እየተካሄደባቸው ናቸው የተባሉት ተጠርጣሪዎችን ብዛትም ሆነ የወንጀል አይነት በተመለከተ ፌደራል ፖሊስ የገለጸው  ነገር የለም።

በቀጣይ በሁለቱም ሀገራት ተፈላጊ የሆኑ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታም ላይ  መወያየታቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ቅዳሜገበያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...