በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ስር በሚገኘው ዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንድ ህጻን የወተት ጥርስ አብቅሎ መወለዱን ተከትሎ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ይህ ክስተት በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመርያው መሆኑ ተገልጿል።
የሆስፒታሉ አዋላጅ ነርስ መንግስቱ ኤባ ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት፤ ምንም እንኳን ህጻናት አብዛኛውን ጊዜ ጥርስ ማውጣት የሚጀምሩት ከ6 ወር በኋላ ቢሆንም፣ አልፎ አልፎ ግን እንዲህ አይነት ክስተቶች (Natal Teeth) ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ አስረድተዋል።
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ አቤ ክስተቱን አስመልክቶ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አብራርተዋል፡
- የበቀለው ጥርስ ለወደፊቱ የህጻኑ ጥርስ አበቃቀል የተስተካከለ እንዲሆን ሲባል በህክምና የሚወገድ ይሆናል።
- ክስተቱ በህጻኑ ጤና ላይ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያመጣ ተረጋግጧል።
- ማህበረሰቡ መሰል ተፈጥሯዊ ክስተቶች ሲያጋጥሙ ሳይደናገጥ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ባለሙያ ማማከር እንዳለበት አሳስበዋል።
Via ዳንግላ ኮሙኒኬሽን
