በጣቷ የምትስለው አርቲስት የአውስትራሊያን የሥነ ጥበብ ሽልማት አሸነፈ

Date:

የፊሊፒን -አውስትራሊያ ዜግነት ያላት አርቲስት ሎሪቤል ስፒሮቭስኪ የአርኪባልድ ሽልማት ያገኘች ሲሆብ የአውስትራሊያ እጅግ የተከበረ የጥበብ ሽልማትን ተቀዳጅታለች።

የአሸናፊነት ስራዋ የአቦርጂናል አውስትራሊያዊ ሙዚቀኛ ዊልያም ባርተን ምስል ሲሆን በጣቶቿ የቀባችው ይህው ስራ የነርቭ ጉዳት ያለባት መሆኑ የሥዕል ስራዋን ከባድ አድርጎታል።

ለብዙ ጊዜ የአርኪባልድ ሽልማት የመጨረሻ እጩ የነበረችው ወይዘሮ ስፒሮቭስኪ ህዝቡ ስራዋን ወዶ በመምረጡ “በጣም ተደስቻለሁ” ብላለች።

በኒው ሳውዝ ዌልስ የስነ ጥበብ ጋለሪ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገረችው “እነዚህ አመታት አስቸጋሪ ነበሩ እናም ይህ አጠቃላይ ልምድ እንዳገኝ እና በስተመጨረሻን ቆንጆ እፎይታ እና ሽልማት ነው” ብላለች

ዊልያም እርሱን እንድስለው ስለፈቀደልኝ እና ለሥራዬ በሚሰጠኝ አስተያየት በጣም ትሑት ስለሆነ ያለማቋረጥ አመስጋኝ ነኝ ብላለች። ወይዘሮ ስፒሮቭስኪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሚስተር ባርተንን ባለፈው ኦክቶበር ሲያገኛት ከነርቭ ጉዳት በማገገም ላይ የነበረች ሲሆን የመሳል ችሎታዋ ተዳክሞ ነበር።

የቁም ሥዕሉ ሲሰራ የሚስተር ባርተንን ሙዚቃ ትጫወት ነበር። “ሙዚቃው ሲጀመር እጄ አነሳና ብሩሹን ወደ ጎን አስቀምጬ ጣቴን ለስላሳ ቀለም ውስጥ እነክር ነበር” ብላለች።

#ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...