በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የመንግስት የህክምና ማዕከላት መካከል አንዱ በሆነው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በመላ ሀገሪቱ ያሉ የጤና ባለሙያዎች የተሻለ ደመወዝ፣ ጥቅማጥቅሞች እና የስራ ሁኔታዎችን በመጠየቅ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ሊያደርጉት ባቀዱት ሀገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ ዋዜማ ዛሬ ሰኞ ማለዳ ላይ ቅድመ የስራ ማቆም አድማ ሰልፍ አካሄዱ።
በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ሰልፍ ላይ የታደሙት የጤና ባለሙያዎቹ “ጤናማ ዜጎች ጠንካራ ኢኮኖሚ ይገነባሉ!”: “ህይወትን እናድናለን የቤት ኪራያችንን ግን መክፈል አልቻልንም” እና “የጤና ሰራተኞች ትንኮሳ ያቁሙ ጥበቃ ይገባናል” የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን ይዘው ታይተዋል።
