በ 2017 በጀት ዓመት ጭማሪ ያሳየው የትራፊክ አደጋ

Date:

በ2017 በጀት አመት የተከሰተው የትራፊክ አደጋ ቁጥር ከ2016 አንጻር ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ ።

በ2016 ዓ.ም ዘጠኝ ወራት 2,248 ሞት ተመዝግቦ የነበር ሲሆን በ2017 ተመሳሳይ ወራት በ2016 ከተመዘገበው የሞት መጠን በ489 ከፍ በማለት  2,722 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል ።

የመንገድና ደህንነትና መድህን ፈንድ ” ጥያቄ ይዘን እንውጣ ” በሚል መሪ ሀሳብ አሳሳቢውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል ።

በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን የሞት ፣ የአካል ጉዳትና የንብረት  ውድመት ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎች  ቢሰሩም አሁንም አሳሳቢ መሆኑ ተነስቷል ።

በኢትዮጵያ ከሚደርሰው የትራፊክ አደጋ 82 በመቶ የሚሆነው በተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ችግር ፣ በአሽከርካሪዎች እና በእግረኞች  የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑ ተገልጿል ።

በተደጋጋሚ አደጋ ከሚያደርሰው ተሽከርካሪዎች መካከል የንግድ ተሽከርካሪዎች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ የሲቪክ ድርጅቶች እና የመንግስት ድርጅት መኪኖች ተከታዩን ደረጃ ይይዛሉ።

በውይይቱ የሲቪል ማህበራዊት ግንዛቤ ከመፍጠር አንስቶ የትራፊክ አደጋን በመከላከልና በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተነስቷል።

እነዚህ ማህበራዊ ከመንግሥት በመቀጠል ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ እና በመቀነስ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ሲሉ የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ጀማል አባሶ ተናግረዋል ።

የትራፊክ አደጋን በዘላቂነት ለመቀነስ መንገድ መሰረተ ልማት ምቹ ማድረግ፣ የትራፊክ ቁጥጥር ስርዓት ማዘመን እና የትራንስፖርት ስርአቱን ማሻሻያ እንደሚገባ ተጠቁሟል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...