ቤተ ሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ ግዙፍ የሕክምና ኮሌጅ ሊያቋቁም ነው

Date:

ከወራት በፊት በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ስራ የጀመረው ቤተ ሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ፣ የራሱን የሕክምና ኮሌጅ ለማቋቋም ማቀዱንና ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።

ተቋሙ በሰንጋ ተራ አካባቢ የሚገነባውን እና እስከ ጥር ወር የሚጠናቀቀውን ዘመናዊ የእናቶችና ሕፃናት እንዲሁም የመካንነት ሕክምና ማዕከልን ጨምሮ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ትልልቅ ከተሞች ቅርንጫፎችን የመክፈት ሰፊ ዕቅድ እንዳለው የዋና ስራ አስፈጻሚው ዶክተር አየለ ተሾመ ማብራሪያ ያመለክታል።

በመግለጫው ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የዋጋ ተመን ቅሬታዎች “ሐሰት” መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የአገልግሎት ዋጋው መካከለኛ ገቢ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል ያማከለና በከተማው ካሉ ውድ ተቋማት አንጻር ሲታይ የሲሶ ያህል ቅናሽ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

ተቋሙ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) የሚጠቀሙና በድምፅ የሚታዘዙ ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎችን የታጠቀ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 25 ሚሊዮን ዶላር (3.5 ቢሊዮን ብር) ወጪ እንደተደረገበት ታውቋል።

በሌላ በኩል፣ ዕውቋ ሞዴል ሃሴት ደረጀ የተቋሙ የመጀመሪያዋ የብራንድ አምባሳደር በመሆን የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አካሂዳለች። ሞዴል ሃሴት በቀጣይ ከተቋሙ ጋር በመሆን በሴቶችና ሕፃናት ጤና፣ በተለይም በጡትና በማኅፀን በር ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ዙሪያ በትኩረት እንደምትሠራ ገልጻለች።

ቤተ ሳይዳ አሁንም የአገልግሎት ጥራቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስመዝገብና የካንሰር ማከሚያ ማዕከል ለማቋቋም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅንጅት እየሠራ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...