ብሪታንያ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት የማህበራዊ ትስስር ገጽ እንዳይጠቀሙ ክልከላ ልትጥል መሆኑ ታውቋል።
አሁን ላይ አንዳንድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻትቦት ለታዳጊ ህፃናት የማይመጥኑና የተቀመጠውን የደህንነት ሕግ የሚተላለፉ መሆኑን ተከትሎ መንግስት በዚህ ዓመት እገዳውን ተግባራዊ አደርጋለሁ ብሏል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር አስተዳደርም ይህን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችለውን ምክክር ያደረገ ሲሆን በወራት ውስጥ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ሬውተርስ አስነብቧል።
እቅዱ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ለታዳጊ ህፃናት የማይመከሩና መቅረብ የሌለባቸው ምስሎችና ሃሳቦች በህፃናቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን ተከትሎ የሚተገበር መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።
ይህም በህፃናት ጥበቃ ድንጋጌ መሰረት የሚተገበር ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም አውስትራሊያ ይህን እርምጃ በመውሰድ ቀዳሚዋ ሃገር መሆኗ ይታወሳል።
ስፔን፣ ግሪክ እና ስሎቬኒያ ይህን መሰሉን እገዳ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል።
ዓለም ላይ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ታዳጊ ህፃናት ላይ አላስፈላጊ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ነው በሚል ጠንካራ እምርምጃ እንዲወሰድ ወላጆች እየጠየቁ ይገኛል።
(አራዳ ኤፍ ኤም)
