በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ አያሌ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት የተመረቀው የአንዱዓለም አራጌ አዲስ መጽሐፍ ብዕርና ባሩድ በአሜሪካ ታትሞ በተለያዩ ከተሞች ለገበያ ቀርቧል።
ብዕርና ባሩድ በአሁኑ ወቅት በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሲልቨር ስፕሪንግ፣ በቨርጂኒያ፣ በሂውስተን፣ በዴንቨር፣ በዳላስ፣ በኦክላንድና ሳንሆዜ በሽያጭ ላይ ይገኛል።
በተጨማሪም በካናዳ ቶሮንቶ ለአንባቢዎች ደርሷል።
በአውሮፓ ደግሞ በጀርመን ፍራንክፈርትና በርሊን፣ በስዊዘርላንድ፣ በሆላንድ አምስተርዳም እንዲሁም በስዊድን ስቶክሆልም ለአንባቢዎች መቅረቡ ታውቋል።
ይህ አዲስ መጽሐፍ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሰንሰለት በጥልቀት የሚፈትሽና ብዙ የሚያወያዩ ቁምነገሮችን የያዘ ሲሆን፣ ለሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄዎችን የሚያመለክት ድንቅ ሥራ መሆኑ ተገልጿል።
መጽሐፉን በኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ የአንላይን ተጠቃሚዎችም በቅርቡ በአማዞን ላይ እንደሚጫን ተጠቁሟል።
