ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ

Date:

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ መክፈቱ ዓለማቀፋዊ ራዕያችንን ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ የቦይንግ ኩባንያ የአዲስ አበባ ቢሮውን በከፈተበት ስነስርዓት ላይ ተገኝተው የቢሮው መከፈት በዓለም አቀፉ አቪዬሽን የኢትዮጵያን እድገት ማሳያ ከመሆን ባሻገር  የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካን እውን የማድረግ አለም አቀፋዊ ራዕያችንን ለማሳካት የሚያግዝ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እያደገ የመጣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አቅም መፍጠሯን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትሩ በብሔራዊ ትራንስፖርት ካውንስል የሚመራ የዘርፉን መሠረተ-ልማት ለማዘመን፣ የትራንስፖርት ንግድ ወጪን ለመቀነስ እና አፍሪካን ለማስተሳሰር የሚያስችል የአስርት አመታት ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

በዘርፉ የ10 አመት የልማት እቅድ ላይም በባቡር፣ በወደብ ልማት፣ በአቪዬሽን እና በስማርት ሎጂስቲክስ ዘርፍ እንደ ቦይንግ ካሉ የግል ሴክተሮች ጋር በጋራ የምንሰራበት የ74 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት እቅድ መቀመጡንም ጨምረው አንስተዋል፡፡

የቦይንግ ኩባኒያ አመራር በኢትዮጵያ ላይ ባሳደረው እምነት አመስግነው ይህንን አጋርነት የአውፕላን ክፍሎችን በማምረት፣ ስልጠናዎችን በመስጠትና በዘላቂ የአቪዬሽን ነዳጅ ላይ በትብብር በመስራት አጋርነታችንን እናሳድግ ብለዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...