ትራምፕ በዩቲዩብ ላይ በመሰረቱት ክስ ቀንቷቸዋል

Date:

ዩቲዩብ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበበትን ክስ ተከትሎ፣ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቱን የአሜሪካው የዜና ወኪል ኒውስማክስ ዘግቧል፡፡

ባለቤትነቱ የጉግል ኩባንያ የሆነው ዩቲዩብ በፈረንጆቹ 2021 በምርጫ ማግስት በዋሽንግተን ሁከት በተነሳበት ማግስት፣ የዶናልድ ትራምፕን አካውንት ለቀናት ዘግቶ እንደነበር ይታወሳል።

በተመሳሳይ ከዩቲዩብ በተጨማሪ ኤክስ እና ፌስቡክም የፕሬዚዳንቱን አካውንት በጊዜያዊነት ማገዳቸው ይታወቃል።

ይህንን የኩባንያዎቹን ውሳኔ ተከትሎ፣ ‘ፖለቲካዊ መድሎ ተፈፅሞብኛል’ በሚል ወደ ፍርድ ቤት ያመሩት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኩባንያዎቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስወሰን ችለዋል።

በዚህም ጥፋቱን አስቀድሞ ያመነው ዩቲዩብ፤ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ኤክስ እና ፌስቡክ በፍርድ ቤት የሚወሰንባቸውን የገንዘብ ካሳ ለፕሬዚዳንቱ እንደሚከፍሉ ይጠበቃል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...