የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ፍጥነት ከነበረው በመጨመሩ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

Date:

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የባቡር ፍጥነት በሰዓት ከነበረበት 37 ኪሎ ሜትር ወደ 60 ኪሎ ሜትር ማደጉን አስታውቋል፡፡የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው÷የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ በቀን የነበረውን የምልልስ መጠን ከሁለት ወደ ስምንት አሳድጓል፡፡፡

የባቡሩ የፍጥነት መጠኑም በፊት ከነበረው በሰዓት 37 ኪሎ ሜትር ወደ በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር ማደጉን አመልክቷል፡፡የባቡሩ ፍጥነት መጨመሩን ተከትሎ ሕብረተሰቡ የፍጥነት መሻሻሉን ባለመገንዘብ ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡

ስለሆነም በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች የባቡሩ ፍጥነት ከዚህ በፊት ከነበረው መጨመሩን በመገንዝብ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማህበሩ አሳስቧል፡፡የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ከዚህ በፊት ጉዳት ሲደርስ ይሰጥ የነበረውን የካሳ ክፍያ ማቆሙንም አስታውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...