“ኑ እንሰባሰብ ” መርሐ ግብር በአሜሪካ ተካሄደ

Date:

“ኑ እንሰባሰብ” በአሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ የቀድሞ የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን በአንድነት ለማሰባሰብና በግቢ ጉባኤ ቆይታቸው የነበረውን አገልግሎት ለማስታዎስና የተፈጠረውን ትስስር ለማደስ ያለመ መርሐ ግብር ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአሜሪካ ማእከል የሕዝብ ግንኙነትና ትብብር እገልግሎት ክፍል አስተባባሪነት ተካሄደ፡፡

በመርሐ ግብሩም የግቢ ጉባኤ መንፈሳዊ ሕይዎት በሦስቱ አስርት ዓመታት  ምን  ይመስል  እንደነበር የተቃኘበት ሲሆን ዘመኑን የሚወክሉ  ለእለቱ መርሐ ግብር የተመረጡ አባላት ትውስታቸውን፤ ልምዳቸውንና ያገኙትን ትምህርት፤ የነበረውን የመደጋገፍ፤ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ሁኔታ በማጋራት ጉባኤተኛውን በትዉስታ ወስደውት ነበር ያመሹት፡፡

እግዚአብሔር ለትውልዱ ያደረገውና የሰጠው የአገልግሎት እድልም ከህሊና በላይ እንደሆነ ከትውስታ ጋር ቀርቧል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ  መርሐ ግብር  ቀጣይ  እንደሚሆን  አባላት ልምዳቸውንና ለክርስቲያናዊ ሕይዎታቸው ማደግ፤ ለሙያ እድገትና ምክክር እንዲሁም ትብብር የሚደግፍ ቀጣይነት ያለው ትስስር ለመገባንት መሠረት ሆኖ እንደሚያገለግል  ከአዘጋጅ ክፍሉ ለማዎቅ ችለናል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...