ኔታንያሁን “ጤና ቢስ (Crazy)” ሲሉ ተሳደቡ ትራምፕ

Date:


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር በነበራቸው የስልክ ልውውጥ በንዴት “ጤና ቢስ (Crazy)” ሲሉ መሳደባቸውን አምነዋል።

ትራምፕ በነበራቸው ቃለ ምልልስ “አዎ ያንን ቃል ተጠቅሜያለሁ ምክንያቱም አሜሪካ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ስትሞክር ቢቢ ሊባኖስ ጋር ሌላ ጦርነት መክፈቱ አበሳጭቶኝ ነው!” ብለዋል።

ፖድ ፎርስ ዋን በተሰኘ ፖድካስት ቆይታ ያደረጉት ትራምፕ በአክሲዮስ የዜና ተቋም፥ ወዳጃቸውን ኔታንያሁ ምስጋና ቢስና ጤና ቢስ ሲሉ ስለመስደባቸው የወጣው መረጃ እውነት ስለመሆኑ ተጠይቀዋል፤

ኔታንያሁ በሊባኖስ ላይ ወታደራዊ እርምጃ በመክፈቱ ትንሽ ተናድጄ ተናግሬያለሁ፥ ነገር ግን አለመስማማቱ እንዳለ ሆኖ አሁንም ጥሩ ወዳጅነታቸው እንዳለ መሆኑን ገልፀዋል ትራምፕ።

አክሲዮስ የዜና ተቋም ስሙን ካልጠቀሰው የአሜሪካ ባለስልጣን አገኘሁት ባለው መረጃ፥ ትራምፕ ከኔታንያሁ ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት በርካታ ሀይለቃሎችን መጠቀማቸውን በሪፖርቱ ይፉ አድርጓል።

ሰኞ እለት አድርገዋል በተባለው የስልክ ልውውጥ ፥ እኔ ነኝ እየታደኩህ ያለሁት ይሄኔ በእስር ላይ ትሆን ነበር፣ ሁሉም ሰው ይጠላሀል እና ሌሎች በርካታ ሀይለ ቃሎችን ተጠቅመዋል ትራምፕ።

ትራምፕ በበኩላቸው ጦርነቱን ለማስቆም ይህንን እና ያንን ማድረግ አለብን ነው ያልኩት ብለዋል።

ሪፖርቱን አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር ያለን ወዳጅነት አልተቀየረም ብለዋል፤

የጋራ ግብ አለን፥ አንዳንድ ጊዜ እንደ ቤተሰብ ሁሉ በአንዳንድ ጉዳይ ያለ መስማማት ይኖራል! ሲሉ ጥያቄውን ያለ ዝርዝር ማብራሪያ አልፈውታል ቢቢ።

ዘገባው የሮይተርስ ነዉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...