ንግድ ባንክ ለዲያስፖራው 50 ቢሊዮን ብር ብድር አዘጋጀ

Date:

  • የባንኩ የብድር አገልግሎቱ ለኢንቨስትመንት፣ ለመኖሪያ ቤትና አውቶሞቢል ግዥ የቀረበ ነው ተብሏል፣

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ሰሞኑን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ፕሬዚደንቱ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በአገር ውስጥ ለሚያካሄዱት የቢዝነስ እንቅስቃሴ፣ ለመኖሪያ ቤትና መሰል ፍላጎቶች የ50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልገሎት ተመቻችቷል፡፡

የብድር አገልግሎቱ በተያዘው የበጀት ዓመት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ባንካችን አገልግሎቱን ለማግኘት ጥያቄ ለሚያቀርቡ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ቀልጣፋና ምቹ አሰራር እንደሚተገብርም አቶ አቤ አስታውቀዋል፡፡
(ኢንባ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...