በሩሲያው ፕሬዝዳንት የተነሱ ዐቢይ ነጥቦች
🟠 የዩክሬን ግጭትን በተመለከተ፦
🔸 በአላስካ ስብሰባ ወቅት የተደረሰው መግባባት ለዩክሬን ሰላም መንገድ ከፍቷል፡፡
🔸 ለዘላቂ እልባት የዩክሬን ቀውስ ዋና መንሣኤ መወገድ አለበት፡፡
🔸 የዩክሬን ቀውስ መነሳት የ”ወረራ” ሳይሆን የመፈንቅለ መንግሥት ውጤት ነው፡፡
🔸 ዩክሬንን ወደ ኔቶ የመቀላቀል የምዕራባውያን ሙከራ የዩክሬን ቀውስ አንዱ ምክንያት ነው፡፡
🔸 የዩክሬን ቀውስ እልባት በመስጠት ሂደት፣ ሩሲያ ማንም ሀገር የራሱን ደህንነት በሌላ ሀገር ኪሳራ ላይ ማረጋገጥ አይችልም የሚለውን መርህ ታስረግጣለች፡፡
🟠 በሻንጋይ ትብብር ድርጀት ውስጥ ስለሚደረግ ትብብር በተመለከተ፦
🔶 በሻንጋይ ትብብር ድርጀት ውስጥ የሚደረግ ምክክር በኢዩኤስያ (በአውሮፓ እና እስያ) ያረጀውን አውሮፓ ማዕከል ያደረገ እና የአውሮፓ-አትላንቲክ ሞዴል የሚተካ አዲስ የደህንነት ሥርዓት መሠረት ለመጣል ያግዛል፡፡
🔶 የሻንጋይ ትብብር ድርጀት ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን በመፍታት ረገድ ያለማቋረጥ ተጽዕኖውን እያሳደገ ነው፡፡
🔶 የሻንጋይ ትብብር ድርጀት ሀገራት መካከል በሚደረግ ንግድ የብሔራዊ መገበያያ ገንዘቦችን በጋራ መገልገል እየጨመረ መጥቷል፡፡
🔶 በሻንጋይ ትብብር ድርጀት ያለው የትብብር እድገት ፍጥነት አስደማሚ ነው፡፡
