ኖቫ ኮኔክሽን ከጊፍት ሪል ስቴት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

Date:

ኖቫ ኮኔክሽን፣ የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እና ግራንድ አፍሪካን ረን አዘጋጅ የሆነው ድርጅት፣ ከጊፍት ሪል ስቴት ጋር ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ።

የኖቫ ኮኔክሽንስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ጋሻው አበዛ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ ሽርክና የዲያስፖራውን ማህበረሰብ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ በባህል ልውውጥ እና በልዩ ስኬቶች እውቅና በመስጠት ለማስተሳሰር ያለመ ነው። ዶ/ር ጋሻው አብራርተው እንደገለጹት፣ ግራንድ አፍሪካን ረን በሺዎች የሚቆጠሩ የዲያስፖራ አባላት በየዓመቱ የሚሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችን በአንድነት የሚያሰባስብና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን የሚያበረታታ ነው። በሌላ በኩል፣ አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በሙያቸው እና በማህበረሰብ አገልግሎታቸው ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች አፍሪካውያን እውቅና የሚሰጥ መድረክ ነው።

የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ እና መስራች የሆኑት አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ፣ ከኖቫ ኮኔክሽንስ ጋር የተደረገውን ስምምነት አስመልክተው ሲናገሩ፣ ጊፍት ሪል ስቴት ከኖቫ ኮኔክሽን ጋር የተደረገው ስምምነት መደሰታቸውን ገልጸው ድርጅቱ በለገሃር፣ በተክለ ሀይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በሲኤምሲ እና በፈረስ ቤት ዘመናዊና ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትመንት መንደሮችን እየገነባ ይገኛል። እነዚህ መንደሮች ትምህርት ቤቶች፣ የህክምና ተቋማት፣ ሞሎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች እና በቂ የመኪና ማቆሚያዎች እንደሚያካትቱ ተገልጿል።

ጊፍት ሪል ስቴት ከዚህ ቀደም የደንበኞችን ፍላጎትና ከጊዜው ጋር የተጣጣመ ዲዛይን እና አዳዲስ እሴቶችን በማካተት ዘመናዊ መንደሮችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉንም አስታውቋል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የጊፍት ሪል ስቴት አምባሳደር የሆኑት የፊልም ዳይሬክተር እና ሙዚቃ ፕሮዲዩሰር አብርሃም ወልዴ ተገኝተው የትብብሩን አስፈላጊነት አድንቀዋል።

ይህ ትብብር ለሁለቱም ድርጅቶች አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ህዝቦች እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚጠቅሙ በርካታ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም የሚያግዝ ይሆናል ብለዋል።


Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) – ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ – በኖቫ ኮኔክሽን የሚዘጋጁ ( የአፍሪካን ኢምፓክት አዋርድ እና የግራንድ አፍሪካን ረን ) ዝግጅቶች የኢትዮጵያ ወኪል ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...