አርሰናል በሊግ ሁለቱ ክለብ ፍሌትውድ ታውን በመለያ ምት 5ለ3 ተሸንፎ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ውጪ ሆኗል።
ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
የፍሌትውድን ግብ ሉፓሎ ቢ ሲያስቆጥር ቪክቶር ዮኬሬሽ አርሰናልን አቻ አድርጓል።
በጨዋታው የአርሰናሉ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማክስ ዶውማን ቀይ ካርድ ተመልክቷል።
ብሩኖ ጉማሬሽ በአርሰናል በኩል የመለያ ምት መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።
በሊግ ሁለት 18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፍሌትውድ ታውን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
አርሰናል ቀጣይ እሁድ ከሊቨርፑል ጋር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።
