አርቴፊሻል ኢንተለጀንትን በመጠቀም ብድር መስጠት ተቻለ

Date:

በአገራችን 49 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ብቻ የባንክ አካውንት አላቸዉ ተብሏል፡፡

ከዚህ በፊት ከየትኛዉም የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ አነስተኛ፣ ጥቃቅን እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እንዲሁም አነስተኛ ይዞታ ያላቸዉ ገበሬዎችን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም ያለማስያዣ ብድር እንዲያገኙ መደረጉን ሰምተናል፡፡

ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ ከ6 ባንኮች ጋር በመተባበር የሚቀርቡ ብድሮችን በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት በማገዝ አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አስታዉቋል፡፡

በክፍያ ቴክኖሎጂስ ባለሙያ የሆኑት ወይንአብ ሳህሉ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፤ አገልግሎቱን እንዲያገኙ የተመረጡት የህብረተሰብ ክፍሎች የባንክ አገልግሎት እየፈለጉ ማግኘት ያልቻሉ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡

ብድር ያለ ማስያዣ ማግኘት አለመቻል፣ የብድር መጠን ፍላጎትም አነስተኛ መሆን አነስተኛ፣ ጥቃቅን እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዦች ብድር እንዳያገኙ ምክንያት ሆነዉ መቆየታቸዉን አንስተዋል፡፡

የኢኮኖሚዉ ከፍተኛዉ አምራች ዘርፍ የሆኑት የጥቃቅን እና አነስተኛ እንዲሁም የግብርናዉ ዘርፍ አባላት ያለ ማስያዣ ብድር ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ ማመቻቸቱንም ተናግረዋል፡፡

በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት በመታገዝ የተበዳሪዎችን የብድር ታሪክ እና የመመለስ አቅም በመለየት ባንኮች ከ35 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ያለ ማስያዣ መስጠታቸዉ ተገልጿል፡፡

ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በጋራ ተግባራዊ የሚያደርገው የዘላቂ የፋይናንስ ተደራሽነት ለኢንተርፕርነርሽፕ ፕሮግራም ከ3መቶ58 ሺህ በላይ ለአነስተኛ፣ ጥቃቅን እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ብድር አቅርቧል።

49 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ብቻ የባንክ አካውንት ያላቸው ሲሆን፤ በሚሊየን የሚቆጠሩ በተለይም የገጠሩ ማህበረሰብ አሁንም ከማንኛውም መደበኛ ወይም ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶች የተገለለ ነዉ፡፡

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ ወጋገን፣ ቡና፣ አማራ፣ እናት እና ዘምዘም ባንክ በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት በመታገዝ ብድር የሚሰጥባቸዉ ባንኮች ናቸዉ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...