አንጋፋው ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ምህንድስና ትምህርት ዘንድሮ ሊጀምር ነው

Date:

ኢትዮጵያ ኑክሌርን ለሰላማዊ አገልግሎት ለመጠቀም ማቀዷን ማሳወቋ አይዘነጋም።

በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የኒውክሌር ምህንድስና ትምህርትን በሁለተኛ ዲግሪ መስጠት እንደሚጀምር የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።  

የኢንስቲትዩቱ የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ዲን ዜናማርቆስ ባንቴ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲሱ የትምህርት ዘመን የኒውክሌር ምህንድስና ትምህርት በሁለተኛ ዲግሪ ሊሰጥ ነው።

በሀገሪቷ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን እንደ አንድ አማራጭ የኃይል ምንጭ አድርጎ የመጠቀም ዕቅድ በመኖሩ ፕሮግራሙን መስጠት ማስፈለጉ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዉ ትምህርቱን  መከታተል የሚፈልጉ ተማሪዎችን እየመዘገበ ሲሆን ለዚህ ትምህርት ብቁ የሚሆኑትም ከዚህ ቀደም በኬሚካል ኢንጅነሪንግ፣ በመካኒካል ኢንጂነሪንግ፣ በኬሚስትሪ፣ በፊዚክስ እና በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸዉ መሆናቸዉን ተናግረዋል።(ኢፕድ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...