አዋሽ ባንክ በአውሮፓውያኑ 2024/2025 ዓመት ከታክስ በፊት 22 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጿል።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው የ2024/2025 የሂሳብ ዓመት አፈፃፀምን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫዉም የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በጀት አመቱ መጠናቀቁን ተከትሎ አዋሽ ባንክ 22 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ከታከስ በፊት ትርፍ ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚዉ በበጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መሰብሰብ መቻሉንም ነዉ ያብራሩት።
ባንኩ በበጀት አመቱ የ106 ቢሊየን ብር የተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡ የተነሳ ሲሆን ይህም ከአምናዉ ጋር ሲነጻጸር የ42በመቶ እድገት እንዳለዉም ተመላክቷል።
የቅርንጫፎቹ ብዛት ደግሞ 989 መድረሱን ዋና ስራ አስፈጻሚው አመላክተዋል።
በበጀት አመቱ ባንኩ 52 አዳዲስ ቅርንጫፎችን እንዲሁም ከ3ሚሊየን በላይ አዳዲስ ደንበኞችንም አፍርቻለዉ ብሏል።
አዋሽ ባንክ የተመሰረተው የዛሬ 30 ዓመት እ.ኤ.አ. ህዳር 10 ቀን 1994 ዓ.ም በ486 መስራች ባለአክሲዮኖች በብር 24.2 ሚሊዮን በተከፈለ ካፒታል ሲሆን፣ መደበኛ የባንክ ስራውን የጀመረው እ.ኤ.አ የካቲት 13 ቀን 1995 ዓ.ም ነው፡፡
በጥቂት ደንበኞች የባንክ አገልግሎት በመስጠት የባንክ ሥራ የጀመረው አዋሽ ባንክ በ30 ዓመት ጉዞው የደንበኞቹ ብዛት ከ15 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ችሏል።
በ137 ሰራተኞች የባንክ ሥራ አንድ ብሎ የጀመረው አዋሽ ባንክ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት የሠራተኞቹ ብዛት ከ20 ሺህ ስድስት መቶ በላይ የተሻገረ ሲሆን የቅርንጫፎች ብዛት ከ989በላይ ደርሷል።
የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን በማጎልበት እና በማዘመን 30 ዓመታትን በላቀ ስኬት የተጓዘው አዋሽ ባንክ ዘመን አፈራሽ የሆነውን እና ለሀገሪቱ የኢንሹራንስ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ያደረገውን የቴክኖሎጂ ውጤት በመጠቀም ለማህበረሰቡ ፈጣን እና አስተማማኝ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት አዋሽ ባንክ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በመመደብ ለተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የማህበረሰብ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን እየደገፈ ይገኛል።
