አፋር ላይ ለቀናት ክልከላ የተደረገባቸው ተሽከርካሪዎች እንዲለቀቁ ተወሰነ

Date:

ሸቀጣሸቀጥ ጭነው ወደ ትግራይ ሲጓዙ በአፋር ክልል ለቀናት ክልከላ የተደረገባቸው ከባድ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ጋር ተወያዩ።

ፕሬዚዳንት ታደሰ ዛሬ ግንቦት 23/ 2017 ዓ/ም ከኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ጋር ባደረጉት ውይይት ባለፉት ጥቂት ቀናት ወደ ትግራይ ሲጓዙ አፋር ላይ ክልከላ የተደረገባቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች የተከለከሉበት ምክንያት የጫኑት ሸቀጣሸቀጥ ከትግራይ አልፎ በኮንትሮባንድ መልክ ወደ ኤርትራ ሊሻገር ይችላል ከሚል ጥርጣሬ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገልጿል።

ሁለቱም ኃላፊዎች ባደረጉት ሰፊ ውይይት ይህ ጉዳይ እውነትነቱ ምን ድረስ እንደሆነ የሚያጣራ ከፌደራል ፖሊስ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ኮሚቴ ጉዳዩን እንዲመረምረው ስምምነት ላይ መደረሱን፣ የኮሚቴው የምርመራ ውጤት መሰረት በማድረግ የቁጥጥር ስርአት እንዲዘረጋ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይህን የማከናወን ተግባርና ኃላፊነት ደግሞ በዋናነት የጋራ ኮሚቴው እንዲሆን ስምምነት ላይ እንደተደረሰና በዚህ መሰረት ተሽከርካሪዎቹ እንዲለቀቁ መግባባት ላይ መደረሱን፣ በቀጣይም ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ኃላፊዎቹ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አውራምባ ታይምስ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ አመልክቷል።

አውራምባ ታይምስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...