አፍሪካውያን መሪዎች እና ምሁራን ለጣና ፎረም ወደ ባሕር ዳር እየገቡ ነው

Date:

ጣና ፎረም በአፍሪካ የደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ የአሕጉሪቷ መሪዎች እና ምሁራን የታላቁ የጣና ሐይቅ መገኛ በኾነው ባሕር ዳር ከተማ ከትመው የሚወያዩበት ከፍተኛ ፎረም ነው።

ፎረሙ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ 11ኛ ፎረሙን በባሕር ዳር እና አዲስ አበባ ከተማ ያካሂዳል።

ባለዘንባባዋ ከተማም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመግባት ላይ የሚገኙ እንግዶቿን ከዋዜማው ጀምራ እየተቀበለች ነው።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች በባሕርዳር ደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው እንግዶችን እየተቀበሉ ይገኛሉ።

የአፍሪካውያን እንግዶች የባሕር ዳር ከተማ ቆይታ ያማረ ይኾን ዘንድ አሥፈላጊው ዝግጅት እንደተደረገም ታውቋል። መረጃው የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...