ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

Date:

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች ኢራንን ለመደብደብ ከአገራቸው ይነሱ እንደነበር ተናገሩ ።

ዩናይትድ ስቴትስ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ግድም ኢራንን ዳግም ስትደበድብ ቆይታ በድንገት ድብደባውን ባለፈው ዐርብ ጋብ አድርጋ አቋርጣለች ። በሁለት ሣምንቱ የኢራን ድብደባ እሥራኤል እንደ ከዚህ ቀደሙ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ተባብራ ድብደባ አልፈጸመችም ።

ምድሯን ለዩናይትድ ስቴትስ ጦር ጄቶች ክፍት በማድረጓ ለሚደርስባት ማናቸውም ጥቃት የአጸፌታ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መኾኗንም ይፋ አድርጋለች ።

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚንሥትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ አገራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በጋራ ኢራን ላይ ጦርነት ከከፈተችበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይመክራሉ ተብሏል ።

እሥራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ ከሔዝቦላህ ጋር የነበራቸውን ጦርነት በተመለከተ ከሊባኖስ ጋር ስለደረሱበት ስምምነትም ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአንጋፋውን ጋዜጠኛ ድምጽ እንደገና እንስማ

ኑ ጥቂት ድጋፍ አድርገን ተስፋ እናለምልም ‼️ ባለ ወርቃማ ድምጹ...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...