“ኢራንን መምታት  አደጋ ነው” ቻይና

Date:


ቻይና” በመካከለኛው ምስራቅ ሰማይ ላይ የጦርነት” ዳመና” ሲያንዣብብ እየታየኝ ነው”  ስትል አስጠነቀቀች።

በመንግስታቱ ድርጅት የቻይና ምክትል ቋሚ ተወካይ በኢራን ዙሪያ ውጥረት እንዲነግስ ማድረግ መካከለኛው ምስራቅን ወደ ግጭት እንደማስገባት ነው ብለዋል።

አሜሪካ በሀይል ጫና ለማሳደር የምትሄድበትን ርቀት እንድታለዝበው ጥሪ አቅርበዋል ተወካዩ።

ሁሉም አካላት ውጥረቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ ቤይጂንግ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጥያቄዋን አቅርባለች።

ዋሽንግተን በግልፅ ቴህራንን ልትመታ እንደምትችል በተደጋጋሚ መግልጫ እያወጣች ነው ፣ ይህም ሰላም አያመጣም በሚልም ቤይጂንግ ከሳለች።

ቻይና ወታደራዊ አማራጮችን እንደማትቀበልም በምክር ቤቱ አረጋግጣለች።

ሀይል መጠቀም ለችግሮች  ፈፅሞ መፍትሄ አያመጣም ቻይና ስትል የሩሲያ ተወካይ በበኩላቸው አሜሪካ የኢራንን የውስጥ ጉዳይ ለፖለቲካዋ እየተጠቀመችበት ነው ሲሉ በፀጥታው ምክር ቤት  ወቅሰዋል።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...