ኢራን ሌሊቱን ለተፈጸመባት ጥቃት አጸፋ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን መታች

Date:

  1. አሜሪካ ተመትቶ ለወደቀው ሄሊኮፕተሯ አጸፋ በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ በባሕረ ሰላጤው አገራት ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን መፈጸሙን የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አስታወቀ።
  2. ሠራዊቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በቀጣናው የሚገኙ የአሜሪካ “አምስተኛው ምድብ ባሕር ኃይል” የራዳር ሥርዓትን እና ጦር ሰፈሮችን በበርካታ ድሮኖች መምታቱን አስታውቋል።
  3. የኢራን ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደዘገበው የአገሪቱ ሠራዊት ጥቃቱን አሜሪካ በደቡባዊ ኢራን ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ለፈጸመችው “ጥቃት” የተሰጠ “የአጸፋ ምላሽ” በማለት በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።
  4. የአሜሪካ ምንጮች ጥቃቱን በተመለከተ ባወጡት ዘገባ ኢራን በአራት ሚሳዔሎች እና በበርካታ ድሮኖች በባህሬን፣ በኩዌይት እና በዮርዳኖስ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ፈጽማለች ብለዋል።
  5. ለኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ቅርብ የሆነው ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው ኢራን በዮርዳኖስ በሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ፈጽማለች።
  6. በዚህም ዋነኛ ዒላማ የነበረው እጅግ ዘመናዊ የሆኑት የአሜሪካ ኤፍ-35 ተዋጊ ጀቶች የሚቀመጡበት መጠለያ መሆኑን ዘቡን ጠቅሶ ዘግቧል።
  7. በተጨማሪም ፋርስ የተባለው የኢራን ዜና ወኪል አብዮታዊ ዘቡ በፋርስ ባሕረ ሰላጤው አካባቢ የሚገኙ “21 የአሜሪካ የአየር እና የባሕር ኃይል ጦር ሰፈሮች ዒላማ ተደርገዋል” ማለቱን ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...