ዳሸን ባንክ 30ኛ የምስረታ ዓመት በዓሉ ማጠቃለያ ላይ ለዲቦራ ፋውንዴሽን 30 ሚሊዮን ብር  ሰጠ

Date:

ባንኩ  በዳሸን ዕድል ጨዋታ አሸናፊ ለሆነ ወጣት የቢዋይዲ ሲግል መኪና አበርክቷል።

የባንኩ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን  ላለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ መርኃ ግብሮች ሲከበር ቆይቷል።

የአከባበር ሥነ ስርዓቱ ማጠቃለያ ፕሮግራም በትናንትናው ዕለት በሸራተን አዲስ ተካሂዷል።

በመርኃግበሩ ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የፋይናንስ ተቋማት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የባንኩ ደንበኞች ተገኝተዋል።

የባንኩን ስያሜ ከማውጣት ጀምሮ የባንኩ ምስረታ ዕውን እንዲሆን ከፍተኛ ዕገዛ ላደረጉት ለሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን የዕውቅና እና የማስታወሻ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለዳሽን ባንክ 11 ባለራዕይ መስራቾች፣ ለቀድሞ የስራ አመራር ቦርድ ኃላፊዎችና ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች፣ አጋር ተቋማት፣ የረዥም ዓመት ደንበኞች እንዲሁም ከዳሸን ባንክ ምስረታ አንስቶ ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ላገለገሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

ዳሽን ባንክ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለዲቦራ ፋውንዴሽን የ30 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በሌላ በኩል በዳሽን ሱፐር አፕ በቀረበውና እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርሱ ሽልማቶች በቀረቡበት የዳሽን ዕድል ጨዋታ የዘመናዊ ቢዋይዲ ሲግል የኤሌክትሪክ መኪና አሸናፊ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...