ኢትዮጵያ በ10 ዓመታት ወደብ ካላገኘች በየዓመቱ 50 ቢሊየን ዶላር ታጣለች

Date:

ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ ወደብ ማግኘት ካልቻለች በየዓመቱ በአማካይ 50 ቢሊየን ዶላር ታጣለች አሉ የኢኮኖሚ ልማትና ኢንቨስትመንት አማካሪ አቶ ደረጀ ደጀኔ።

አማካሪው ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት÷ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ እድገት እየታየበት ነው።

በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዓመታዊ ጥቅል ምርቷ 1 ትሪሊየን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል ይገመታል ያሉት አቶ ደረጀ÷ የወጪና ገቢ ንግዱ ደግሞ የዚህን 50 በመቶ ድርሻ እንደሚሸፍን አመላክተዋል፡፡

አሁን ከወደብና ወደብ ጉዳዮች ጋር ተያይዘው ላሉ ወጪዎች እያወጣን ያለነው የውጪና ገቢ ንግዱን 10 በመቶ እንደሆነ አንስተዋል።

በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ ይህ የክፍያ መጠን ምንም ሳይጨምር ቢቆይ እንኳን ኢትዮጵያ በዓመት 50 ቢሊየን ዶላር ታጣለች ነው ያሉት።

ይህም እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ 10 ግድቦችን መገንባት የሚያስችል ሀብት በየዓመቱ እንድናጣ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በቀጣይ ዓመታት የባሕር በር የማናገኝ ከሆነ የሀገርን ሀብት ባሕር ላይ ወርውሮ እንደመመለስ ነው ሲሉም ባሕር በር የማግኘትን ጥቅም አጽንኦት ሰጥተዋል።
(ኤፍ ኤም ሲ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ ለኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ደብዳቤ ላከች

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ለኢራን ብሔራዊ ደኅንነት ምክር...

ዓመታዊ ግብርን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ማሳወቅና መክፈል የሚያስችል አዲስ አሰራር ተዘረጋች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ከእንግዲህ የደረጃ «ሀ» ግብር...

62ኛው የባህል ማዕከል ምሽት አንጋፋዋን ጋዜጠኛ የመዓዛ ብሩን ዘክሯል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፥ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ...

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ሀኪም ቁጥር አራት ብቻ ናቸው

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በሰፊው እንደሌለ እና...