ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የ4.1 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የሽሬ እና የጎንደር ሆስፒታሎችን የጤና አጠባበቅ አገልግሎት ለማጠናከር የሚውል የ4.1 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ ፈርመዋል።

በዚሁ ወቅት ንግግር ያደረጉት አቶ አሕመድ ሺዴ፤ ስምምነቱ በተለይም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚጠቅም ገልፀዋል።

በስምምነቱ መሰረት የሚከናወኑ ሥራዎችም ከ15 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሚቀርበውን የጤና አጠባበቅ አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚያግዙ ተናግረዋል።

በተለይም እናቶች በደህና እንዲወልዱ፣ ሕጻናት ሕይወት አድን እንክብካቤ እንዲያገኙ እና ተፈናቃዮች አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ሲሉ መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...