ኢዜማ የሊቀመንበር ምርጫ ሊያደርግ ነው

Date:

ዕጩ ተወዳዳሪዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ጀምረዋል

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባኤውን  በመጪው  ሰኔ 28 እና 29 ቀን  2017 ዓ.ም. የሚያደርግ  ሲሆን፤ በዚህ ጠቅላላ ጉባኤም የከፍተኛ አመራሮች ምርጫ እንደሚካሄድ ፓርቲው አስታውቋል፡፡

በጠቅላላ ጉባኤው የሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀ መንበር እንዲሁም  የዋና ጸሐፊና ፋይናንስ  ኃላፊ ምርጫ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በዚሁ መሠረት ባለፉት ወራት የእጩዎች ልየታ የተደረገ ሲሆን፤ በትናንትናው ዕለት ሰኔ  2 ቀን  2017 ዓ.ም. ለኃላፊነት የሚፎካከሩ ተወዳዳሪዎች የፓርቲውን የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ተጠቅመው የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚያካሒዱበትን ዕጣ ማውጣታቸውን ፓርቲው ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የውድድርና የምረጡኝ ቅስቀሳ የስነ- ምግባር ደንብ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል ተብሏል፡፡

ዕጩ ተወዳዳሪዎቹ ከሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያካሂዱ አስመራጭ ኮሚቴው አሳውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...