እምነት ወደ ተግባር የተሸጋገረ የዜግነት ኃላፊነት፡ ወጣቶች እና የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ የነገ ዕጣ ፈንታ

Date:

5 .ለመራጭነት ለመመዝገብ ምን ያስፈልጋል? ተግባራዊ መመሪ

ግዮን መጽሔት :- ወጣቶች ራሳቸውንና ሌሎችን ለማስተባበር፣ ለመመዝገብ ምን እንደሚያስፈልግ በግልጽ ማወቅ እና መረጃውን ማሠራጨት አለባቸው። ምንም እንኳን ዝርዝር የሕግ መመሪያዎቹን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየወቅቱ የሚያወጣቸው ቢሆንም፣ በአጠቃላይ የዜግነት ተሳትፎ ሥርዓት ሲታይ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለመመዝገብ የሚከተሉትን መሠረታዊ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል።


ዕድሜ እና ዜግነት፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው እና በምዝገባው ወቅት ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ ዜጋ የመምረጥ ሕገ-መንግሥታዊ መብት አለ።·

መታወቂያ እና ማረጋገጫ፡ ማንነትን የሚገልጽ ሕጋዊ መታወቂያ መያዝ ግድ ነው። ይህ የቀበሌ/የወረዳ ነዋሪነት መታወቂያ፣ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ፓስፖርት፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የጡረታ መታወቂያ፣ ወይም በምርጫ ቦርድ ሕግ እውቅና የተሰጠው ማንኛውም ሕጋዊ ሰነድ ሊሆን ይችላል።·

የምዝገባ ቦታ እና ቆይታ፡ ምዝገባው የሚካሄደው ዜጎች ለተወሰነ ጊዜ በነዋሪነት በቆዩበት አካባቢ (ቀበሌ/ወረዳ) በተዘጋጁት ሕጋዊ የምዝገባ ጣቢያዎች ነው።·

በአካል መገኘት፡ መታወቂያን ይዞ በአካል በምዝገባ ጣቢያ መገኘት እና በምርጫ አስፈጻሚዎች የሚሰጠውን ቅጽ መሙላት፣ እንዲሁም የመራጭነት ካርድን በቦታው ተገኝቶ መቀበል ያስፈልጋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዚህኛው ምርጫ በአዲስ አበባና በተመረጡ አካባቢዎች ወደ ምዝገባ ጣቢያ በአካል መሄድ ሳይስፈልግ በእጅ ስልካችን የመመዝገብ አማራጭ ያለ መሆኑ ጭምር መረዳት እና ማስረዳት ይገባል።

ወጣቶች እነዚህን መረጃዎች በየአካባቢያቸው ለሚገኙ ሰዎች፣ በተለይም የቴክኖሎጂና የመረጃ ተደራሽነት ለሌላቸው፣ ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ እንዲሁም ዕድሜያቸው 18 ሞልቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅ ለሚሰጡ ታዳጊ ወጣቶች (First-time voters) በማካፈል የተግባር መመሪያና ድጋፍ (Civic Guidance) ሊሰጡይገባል።

6. ወጣቶች የዴሞክራሲያዊ ሰላም ግንባታ ዋልታዎች እን
ደመሆና
ቸውምርጫዎች (በተፈጥሯቸው) የፖለቲካ ውድድር፣ የሐሳብ ፍጭት፣ የፖሊሲ አማራጮች ክርክር እና የድጋፍ ማሰባሰብ የሚታይባቸው ሂደቶች ናቸው። በዚህ የፉክክር ሂደት ውስጥ፣ የፖለቲካ ትኩሳት ሊጨምር ይችላል። ይሁን እንጂ፣ ይህ የሐሳብ ውድድር ወደ አላስፈላጊ የሰላም መደፍረስ፣ የእርስ በርስ መቃቃር፣ እና አካላዊ ግጭቶች እንዳይቀየር ወጣቱ ግንባር ቀደም ሚና አለው።

ወጣቶች የፖለቲካ ኃይሎች መሣሪያ፣ የጥላቻ ፖለቲካ አስፈጻሚዎች ወይም የግጭት ማራገቢያ ከመሆን ይልቅ፣ የዴሞክራሲያዊ ሰላም ግንባታ ዋልታዎች መሆን አለባቸው።አንድ ወጣት በምርጫ ሂደቱ ውስጥ ሰላማዊ ተሳትፎ ሲያደርግ የሚከተሉትን እሴቶች በተግባር
ያሳያል፡

1. የመቻቻል ባህልን ማዳበር፡ የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት፣ በምክንያት እና በማስረጃ የማስተናገድ ባህልን ያዳብራል። የሌላውን ሐሳብ ባይደግፈውም የመደመጥ መብቱን ያከብራል።

2. የሐሰተኛ መረጃዎችን (Misinformation/Disinformation) መዋጋት፡ በዘመነ-ዲጂታል የጥላቻ ንግግሮችንና በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሱ ሐሰተኛ መረጃዎችን በጥንቃቄ ይመረምራል፤ እውነትነታቸውን ሳያረጋግጥ ከማሰራጨት ይቆጠባል።

3. የሕግ የበላይነትን ማክበር፡ የምርጫ ሕጎችን፣ የሥነ-ምግባር ደንቦችን እና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ያከብራል። በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ ሥርዓት አልበኝነት እንዳይነግሥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋ
ር ይተባበራል።

4. ውጤትን በጸጋ መቀበል፡ የምርጫውን ውጤት (አሸናፊነትንም ሆነ ተሸናፊነትን) በጸጋ የመቀበል ባህልን ያዳብራል። ቅሬታ ካለ በሕጋዊና በሰላማዊ መንገድ ብቻ (በፍርድ ቤት ወይም በምርጫ ቦርድ በኩል) የማቅረብ ኃላፊነት የሚሰማው ዜግነትን (Responsible Citizenship) በተግባር ያሳያል።

ወጣቶች የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጠባቂዎች (Guardians of Democracy) ናቸው። ወጣቶች በምርጫ ጣቢያዎች በታዛቢነት፣ በመራጭነት፣ ድምፅ በመስጠት፣ እና ሰላምን በማስከበር በጎ ፈቃደኛነት የሚያደርጉት ተሳትፎ፣ አገራችን ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን እንድትገነባ የማይተካ አስተዋጽኦ አለው። የሰላም ዋጋ ከምንም ነገር በላይ፣ የዴሞክራሲም ዋጋ በሰላም ላይ የቆመ መሆኑን በመገንዘብ፣ ወጣቱ ምርጫን እንደ ጦርነት አውድማ ሳይሆን እንደ ሐሳብ ገበያ አድርጎ ሊወስደው ይገባል።

7. ማጠቃለያ፡ ለኃላፊነት የተሞላበት የዜግነት ተሳትፎ የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ወጣቶች ሆይ! የነገዋ ኢትዮጵያ የምትገነባው፣ የምትዋቀረው እና የምትተዳደረው ዛሬ በምትወስኑት ውሳኔ እና በምታደርጉት ተግባራዊ ተሳትፎ ነው። አባቶቻችን እና እናቶቻችን አገራችንን በነጻነት አቆይተው አስረክበውናል። እኛ ደግሞ ዴሞክራሲያዊት፣ ፍትሐዊት እና የሁሉም ዜጎቿ መብት በእኩልነት የተረጋገጠባትን አገር የመገንባት የታሪክ አደራ አለብን።

7ኛው አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ፣ አገራችንን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ፣ የሰላም እና የብልጽግና ምዕራፍ ለማሸጋገር የተፈጠረ ወርቃማ ዕድል ነው። ይህ ዕድል ግን ወደ እውነትነት የሚለወጠው እናንተ በንቃት፣ በብዛት እና በኃላፊነት ስትሳተፉ ብቻ ነው።

ዴሞክራሲያዊ አገርን መመኘት ብቻውን በጭራሽ በቂ አይደለም፤ ምኞትን ወደ ተግባር፣ ተስፋን ወደ እውነታ መቀየር ያስፈልጋል። የመራጭነት ካርዳችሁን ዛሬውኑ አውጡ! መመዝገቢያ ጊዜው ሳያልፍ፣ ለነገ ሳትሉ ፈጥናችሁ ወደ ምዝገባ ጣቢያዎች አቅኑ! እናንተ ብቻ መመዝገብ ሳይሆን፣ ጓደኞቻችሁን፣ ቤተሰቦቻችሁን፣ የሥራ ወይም የትምህርት ተቋም ባልደረቦቻችሁን እና አብረዋችሁ የሚኖሩትን ዜጎች ሁሉ በማስተባበር፣ በማነሳሳት እና በመርዳት ወደ ምርጫ ጣ
ቢያ ይዟቸው ውጡ።

ድምጻችሁ ኃይላችሁ፣ ካርዳችሁ ደግሞ የመጻኢው ዘመን መወሰኛ መሣሪያችሁ ነው። በሰላማዊ መንገድ አገራችሁን የማገልገል፣ የመገንባት፣ እና የመምራት የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ፣ የታሪክን ጥሪ እንድትቀበሉ አገራዊ ጥሪያችንን በታላቅ አክብ
ሮት እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አቅጣጫ እና ብሩህ ተስፋ ያለው በነቃው ወጣቶቿ እጅ ላይ ነው!

ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው በወጣቶች እና ባህል ልማት ፋውንዴሽን (Youth and Cultural Development Foundation – YCDF) ከ አውሮፓ ኅብረት (EU)  ጋር በመተባበር ነው። የወጣቶች እና ባህል ልማት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት፣ ባህላዊ እሴቶችን በማሳደግ፣ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በማስፋፋት እና የወጣቶችን ንቁ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ በማጎልበት ላይ በትኩረት የሚሠራ ገለልተኛ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ወጣቶች በሀገር ግንባታ ሒደት ውስጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ግንዛቤ በመፍጠርና አቅማቸውን በማጎልበት የላቀ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ግዮን መጽሔት ቅጽ 8 ቁጥር  230 መጋቢት 2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...