እስራኤል በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶቿ ስልክ መጠቀምን ልታግድ ነው

Date:

የእስራኤል የትምህርት ሚኒስቴር ከመጪው የካቲት ወር ጀምሮ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስልክ መጠቀምን አግዷል።

በእስራኤል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የሚባለው ከ1-6 ክፍል ያለው ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ትኩረት ለመጨመር እንደዚሁም የማህበራዊ እና የስሜት ክህሎት እንዲያዳብሩ ለማድረግ ሲባል በትምህርት ቤቶች ስልክ መጠቀምን ማገዱን አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዮኣቭ ኪሽ ተማሪዎቻችን ያለ ስክሪን እውነተኛ ግንኙነት እንዲኖራቸው እንፈልጋለን ያሉ ሲሆን ውሳኔው ሰፊ ጥናት ከተሰራ በኋላ የመጣ ነው ብለዋል።

ዩኔስኮ በ2024 መጨረሻ 40 በመቶ በሚሆነው የአለማችን የትምህርት ስርዓት ውስጥ ስልክ መጠቀም መታገዱን አስታውቋል።

ብራዚል፣ ቺሊ፣ ፈረንሳይ፣ ሃንጋሪ፣ ኔዘርላንድስ፣ ቻይና እና የተወሰኑ የአሜሪካ ግዛቶች በተለያየ ደረጃ በትምህርት ቤቶች ስልክ መጠቀምን ከልክለዋል።

በኢትዮጵያም፥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ዓመቱ መጀመሪያ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ  ስልክ ፣ ታብሌት እና የመሳሰሉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን በፍጹም ይዘው መገኘት እንደማይችሉ እና ይህን ቢያደርጉ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል መግለጹ ይታወሳል።

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ባዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ በትምህርት ቤትና አካባቢ ሞባይል፣ ታብሌት እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ በመገኘት ከትምህርትና ትምህርት አዘል ፕሮግራሞች ውጭ መጠቀም መከልከሉን ይጠቅሳል።

ዘገባው የታይምስ ኦፍ እስራኤል ነው።

😀|@tikvahethmagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...