እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት እየፈጸመች ነው

Date:

ሁለት ስመ ጥር የእስራኤል የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት እየፈጸመች እንደሆኑ አስታወቁ።

‘ቤትሰሌም’ እና ‘ፊዚሻን ፎር ሂውማን ራይትስ እስራኤል’ የተሰኙት በእስራኤል ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ ተቋማት የጋዛን ጦርነት አስመልክቶ ባወጡት ሪፖርት እስራኤል በፍልስጤም ሕዝብ ላይ እየፈጸመችው ያለው ድርጊት በዘር ፍጅትነት የሚፈረጅ ነው ብለዋል።

የመብት ቡድኖቹ ያለፉትን 21 ወራት የጋዛ ጦርነት አስመልክቶ ያደረጓቸውን ጥናቶች ሰኞ፣ ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም ይፋ አድርገዋል።

በእስራኤል ውስጥ መቀመጫቸውን ለአስርት ዓመታት ያደረጉት እና በንቁ ተሳትፏቸው የሚታወቁት ተቋማቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ “ወንጀሎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጥሪ ከማድረግ በተጨማሪ፤ በዚህ የጨለማ ወቅት ድርጊቶችን በስማቸው መጥራት መሠረታዊ ጉዳይ ነው” ብለዋል።

እስራኤላውያኑ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች አገራቸው “በፍልስጤማውያኑ ላይ የዘር ፍጅት እየፈጸመች ነው” በሚል ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጡትን ሪፖርት የእስራኤል መንግሥት ቃል አቀባይ ውድቅ አድርገውታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...