እንግሊዝ የሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ  ሻምፒዮን ሆነች

Date:

በሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ እንግሊዝ ስፔንን በመለያ ምት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆናለች።

አንድ ሰዓት ላይ በባዝል በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች የተገናኙበት  መደበኛ 90 ደቂቃ አንድ አቻ ተጠናቋል።ለሁለቱም ቡድኖች የአርሰናል ተጫዋቾች ግቦቹን አስቆጥረዋል።

34ሺህ ተመልካቾች በታደሙበት ሴንት ጃኮብ ፓርክ ስቴዲየም ማሪዮና ካልዴንቲ ለስፔን እና አሊሲያ ሩሶ ለእንግሊዝ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

አሸናፊውን ለመለየት በተጨመረው 30 ደቂቃ ግብ ባለመቆጠሩ  ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት አምርተዋል።

በተሰጠው መለያ ምትም እንግሊዝ 3 ለ 1 አሸንፋለች። የ2022 የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋ እንግሊዝ በተከታታይ ለ2ኛ ጊዜ የአህጉሩ ሻምፒዮን ሆናለች።

በሲውዘርላንድ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው ድግስ የአውሮፓ ዋንጫን አንስታ የማታውቀው የዓለም ሻምፒዮኗ ስፔን፤ ከዚህ ክብር ጋር ለመጀመርያጊዜ የምትገናኝበትን አጋጣሚ ሳትጠቀምበት ቀርታለች።

ሁለቱ ሀገራት በ2023 በተገናኙበት የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ስፔን 1 ለ0 አሸንፋ ዋንጫውን ማንሳቷም ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...