የትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የመንግስት ከፍቸኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የአፈፃፀም ውል ለማድረግ እና ተቋማዊ አሰራርን በጥብቅ ለመከታተል የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን አስታውቋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አፈፃፀም እና የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ አዳዲስ የአሰራር ተግባራዊ መደረጉን የተናገሩት በትምህርት ሚኒስቴር የበይነመረብ ትምህርት ማጠናከር ፕሮግራም ዋና አማካሪ ዶክተር ጌታሁን መኮንን ናቸው።
አዲሱ አሰራር ትኩረቱን በዩኒቨርሲቲዎች አጠቃላይ የትምህርት እንቅስቃሴ ላይ የሚያደርግ ሲሆን፣ በየዓመቱ መጀመሪያ ላይ የመምህራን እና የተማሪዎች አጠቃላይ የትምህርት እቅዶች በተቋማዊ እቅድ ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል ብለዋል።
አክለውም ፤ከሀገር አቀፍ አጠቃላይ ግምገማዎች ጎን ለጎን የተቋማቱን እንቅስቃሴና አፈፃፀም በቅርበት የሚከታተልና የሚገመግም ልዩ የክትትልና ግምገማ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል
አሐዱ ሬዲዮ
ከመንግስት ከፋተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ውል ሊደረግ ነዉ
Date:
