ከኒውክሌር በተጨማሪ የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ስጋት እንደሆነባት አሜሪካ ገለጸች

Date:

ኢራን ካላት የኒውክሌር መረሃ ግብር በተጨማሪ ያሏት ተወንጫፊ ሚሳዔሎች እና የባሕር ኃይል ሠራዊቷ ከባድ የደኅንነት ስጋት ናቸው ስትል አሜሪካ ገለጸች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የትራምፕ ከፍተኛ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሆኑት ማርኮ ሩቢዮ “ለረዥም ጊዜ የአሜሪካ ስጋት ሆና የቆየችው ኢራን አሁንም አሳሳቢ ሆና ቀጥላለች” ብለዋል።

ከአሜሪካ ጋር በምታካሂደው የኒውክሌር ግንባታ ዙሪያ ሦስት ድርድሮችን ያደረገችው ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ አገለግሎት ብቻ የሚውል ነው ስትል በተደጋጋሚ ስታስተባብል ቆይታለች።

ባለፈው ሰኔ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተፈጸመባት ኢራን “የኒውክሌር ማዕከላቷ ከወደሙ በኋላ መልሳ እንዳትገነባ ተነግሯት ነበር። ነገር ግን አሁንም መልሰው ለመገንባት እየሞከሩ ማሆናቸው ይታያል” ያሉት ሩቢዮ፤ “አሁን ዩራኒየም እያዳበሩ ባይሆንም፣ እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ እየሠሩ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ከኒውክሌር ፕሮግራሟ በተጨማሪ ኢራን ረዥም ርቀት መጓዝ የሚችሉ በርካታ ሚሳዔሎች እንዳሏት እና ይህም በአሜሪካ እና በአጋሮቿ ላይ ከባድ አደጋን የሚደቅን እንደሆነ አክለዋል።

ይህ የኢራን የተወንጫፊ ሚሳዔሎች ፕሮግራም በተለይም አጭር ርቀት የሚጓዙት “በቀጣናው ያሉትን የአሜሪካ አጋሮች እና የጦር ሰፈሮችን ዒላማ የሚያደርጉ ናቸው” ብለዋል።

አሜሪካ በኢራን ዙሪያ ያሉት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ኳታር እና ባህሬን ዋነኛ ወዳጆቿ ሲሆኑ ወታደራዊ ሰፈርም አላት። ሩቢዮ ጨምረውም የኢራን የባሕር ኃይል አቅም አሳሳቢ መሆኑን እና “የንግድ መርከቦችን እና የአሜሪካንን የባሕር ኃይል አባላትን ዒላማ ሊያደርጉ ይችላሉ” ብለዋል።

ኢራን ከኒውክልር ፕሮግራሟ ውጪ በሚሳዔሎቿ ላይ ከአሜሪካም ጋር ሆነ ከሌላ ወገን ጋር የመነጋገር ፍላጎት እንደሌላት እና ይህንንም “ትልቅ ችግር” ሲሉ ገልጸውታል።

“ሁሉም እንዲያውቀው የምፈልገው ኢራን ከኒውክልር ፕሮግራሟ ባሻገር በዋናነት አሜሪካንን ለማጥቃት የሚውሉ መደበኛ የጦር መሣሪያዎች አላት። ጥቃት ለመፈጸም የሚወስኑ ከሆነ ግን ጉዳዩ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

“በአገራቸውን እና በኢራን መካከል የሚደረገውን ድርድር በተመለከተም፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲገኝ እንደሚፈልጉ ነገር ግን ንግግሩ የማይሳካ ከሆነ ሌሎች አማራጮች ክፍት መሆናቸውን አመልክተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...