ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር እንዲሆን ተወሰነ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ትላንት አመሻሽ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከነዚህም አንዱ፥ በፕላንና ልማት ቢሮ እና በት/ት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበውን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር የማድረግ ነው።

ካቢኔው “በአካባቢው ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት፣ የምርምር፣ የእውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ የመንደር ምስረታውን ዉሳኔ ፀድቋል” ሲል አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ፦

  • የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና ፤ የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል።
  • በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች፤ የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶም ዉሳኔ አስተላልፏል።
  • የምግብ ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይም ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...