ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣትና ከጨረታ ሽያጭ ከ290 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ

Date:

በ2017 በጀት ዓመት በ9 ወራት ውስጥ ከደምብ ተላላፊዎች ከተወረሱ ቁሳቁሶች የጨረታ ሽያጭ እና ከደምብ ተላላፊዎች ቅጣት በድምሩ ከ290 ሚሊዮን 543 ሺሕ ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡  

ከዚህም መካከል ደንብ ቁጥር 167፣ 150 እና 180/2017ን ተላልፈው ከተገኙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከ258 ሚሊዮን 800 ሺሕ ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን፤ ከ17 ሚልዮን 200 ሺሕ ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ ከደንብ ተላላፊዎች ተወርሰው በጨረታ ከተሸጡ ንብረቶች የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት 9 ወራት ከጨረታ ሽያጭና ከቅጣት ከ290 ሚሊዮን 543 ሺሕ ብር በላይ ተሰብስቧል።

ከተሰበሰበው ገንዘብ ከ268 ሚሊዮን 322 ሺሕ ብር ለፋይናስ ገቢ ሲደረግ፤ ከ22 ሚልዮን 221 ሺሕ ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ባለስልጣኑ ሕገ-ወጥ የጎዳና ንግድ ሲያከናውኑ የተገኙ 34 ሺሕ 260 አካላት ላይም እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

በቅርብ ጊዜያት ደምብ ተላላፊዎች ላይ የቅጣት እርምጃ የሚወስዱ በርካታ ሕግና ደንቦች መውጣታቸውን ያነሱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፤ በተለይም በደንብ ቁጥር 167 ላይ የተመለከተው ከፅዳት ጋር የተያያዘ መመሪያ ከፍተኛ ቅጣት የሚያስከትል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የወንዞችንና የወንዝ ዳርቻዎችን ከቆሻሻና ብክለት ነፃ ለማድረግ የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 በሚገባ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም ሕግና ደንቦች በሚወጡበት ሰዓት ገቢ ለመሰብሰብ ሳይሆን፤ ትልቁ ነገር የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሕግና ደንብን ለማስፈፀም ከጸጥታ መዋቅርና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝና ደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...