ከፈንታሌ ወረዳ ስድስት ሰዎች በኮሌራ በሽታ ህይወታቸው አለፈ

Date:

በኦሮሚያ ክልል በፈንታሌ ወረዳ በመሬት በተከሰተው መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ ስድስት ሰዎች በንፁህ ውሃ እጦት ምክንያት በተከሰተ የኮሌራ በሽታ መሞታቸውን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አሰቦት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

ኃላፊው ተፈናቃዮቹ ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማጣታቸው የዝናብ ውሃን ለመጠጥነት እየተጠቀሙ መሆኑን በመግለጽ፤ “በርካታ ሰዎች በኮሌራ በሽታ ተይዘው ስድስት ሰዎች ሞተዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ፤ “ከዚህ ቀደም እርዳታ በቡሳ ጎኖፋ እና በእርዳታ ድርጅቶች በኩል ይሰጥ ነበር” ሲሉ ገልጸው፤ አሁን ግን ሲደረግልን የነበረው እርዳታ “ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል” ብለዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በ አፋር ክልል እንደ ዱለቻ እና አዋሽ ፋንታሌ ካሉ ወረዳዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በእርዳታ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል።

ከአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ መፈናቀላቸውን የተናገሩት መሀመድደወል ኦስማን፤ “የሰብዓዊ እርዳታ ቢያንስ ላለፉት ሶስት ወራት ተቋርጧል” ሲሉ ጠቅሰው፤ ተፈናቃዮቹ በምግብ እና የመጠጥ ውሃ እጦት ችግር ውስጥ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...