በኢትዮጵያ የነርቭ ዘንግ ችግር የሌለባቸውን ልጆች መውለድ የሚችሉት 29 በመቶ ሴቶች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።
ከ10 እናቶች መካከል 6ቱ የነርቭ ችግር ያለባቸውን ህፃናት ሊወልዱ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አጥኚ ዶክተር ማስረሻ ተሰማ ገልፀዋል።
የበሽታው ምክንያትም ምግብን በጠቃሚ ንጥረ ነገሮች አለማበልፀግ መሆኑ ተመላክቷል። ይህ የጤና ችግር ዜጎች የተስተካከለ የሰውነት ክፍል እንዳይኖራቸው ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል።
የነርቭዘንግ ችግር ከተሰኘው የበሽታ አይነት ጋር በተያያዘ በዓመት ከ30 ሺሕ በላይ ህፃናት እንደሚወለዱ የሆፕ ኤስ ቢ ኤች ስራ አስኪያጅ ቤዛ በሻህ ገልፀዋል።
በበርካታ ሆስፒታሎች ህክምናው አለመኖሩ እና ዜጎች ቅድመ መከላከል ላይ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን የበርካታ ህፃናት ህይወት እንደሚጠፋ ምክንያት መሆኑን ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል።
የበሽታው ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦች ሽንት መቆጣጠር የማይችሉ እና በራሳቸው መንቀሳቀስ የሚያዳግታቸው እንደሆኑም ተገልጿል።
(ሀገሬ ቴቪ)፤
