- ሲሸጡና ሲጠቀሙ በተገኙ ላይ እርምጃ ይወሰዳል – ባለሥልጣኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን፣ በአዋጅ 11/12 2011 መሰረት፣ ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ትንባሆ ሲሸጡና ሲጠቀሙ ከተገኙ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡
በባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው እንደተናገሩት፤ አዲስ አበባን ከትምባሆ ጭስ ነፃ ለማድረግ በተቀረፀው መደበኛ ቁጥጥር መሰረት፣ የጤና ተቋማትን፣ የህዝብ መሰብሰቢያ ስፍራዎችንና የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ከትምባሆ ጭስ ነፃ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
“በትምባሆና በኒኮቲን ምርቶች ላይ የትምባሆ ኢንዱስትሪ ስልቶች ማጋለጥ” በሚል መሪ ቃል ሜይ 31 የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀንን በማስመልከት ከተማ አቀፍ የፀረ-ትምባሆ ንቅናቄ ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡
