በኤች አይቪ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ፈያ ኢንቴግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን (FIDO) ይህንን ያስታወቀው የ2024 ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው።
ድርጅቱ በአዲስ አበባ በኦሮሚያ በጅማ በአፋርና በሌሎችም ክልሎች በቫይረሱ ለተጠቁ ዜጎችና ወላጆቻቸው ላጡ ህጻናት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም ሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉንም ገልጿል።
ድርጅቱ ከዩ ኤስ ኤይድ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ባለፉት ዓመታት በነበረው የጸጥታ ችግር ተጋላጭ የነበሩ ወገኖች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ የሴቶችና ልጃገረዶች ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስና የውሃ ማከሚያ ኬሚካሎችና ሌሎች የቤት መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፎች ማበርከታቸውን አክለው ገልጸዋል።
በድጋፉ በተለይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸውን ዜጎች በመለየትና ተደራሽ ማድረግ እንደሆኑ ገልጸው፣ ድርጅቱ እነዚህን ወገኖች በዘላቂነት ለማቋቋም እገዛውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ፈያ በቀጣይ 2025 የስራ እቅዱ ለ197ሺህ ያህል ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱንም ነው የገለጸው።
