ከ9 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል

Date:

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እስካሁን ድረስ 9 ሚሊዮን 36 ሺህ 994 ዜጎች ለመራጭነት መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ማምሻውን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፣ ከዚህ ውስጥ ከ600 ሺህ የሚሆኑት መራጮች “ምርጫዬ” በተሰኘው ዘመናዊ መተግበሪያ አማካኝነት የተመዘገቡ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቋቋሙት 52 ሺህ 773 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ46 ሺህ 757ቱ ላይ የመራጮች መመዝገቢያ ቁሳቁሶች በወቅቱ ደርሰው ምዝገባው በስኬት እየተካሄደ መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ 6 ሺህ 395 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በጸጥታ ሥጋትና ቁሳቁስ በወቅቱ ባለመድረሱ ምክንያት እስካሁን ምዝገባ እንዳልጀመሩም ተጠቁሟል።

ቦርዱ ለምርጫው ሂደት 187 ሺህ 28 አስፈጻሚዎችን ያሰማራ ሲሆን፣ የምርጫ ጣቢያዎችን እንቅስቃሴ በጥብቅ እየተከታተለ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል፣ ምርጫው ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን በትኩረት እየሠራ መሆኑን የገለጸው ቦርዱ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆነው በተገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

በተደረገው ማጣራት ከአስፈጻሚነት ከተሰናበቱት ግለሰቦች መካከል ከፓርቲ አባልነት ባለፈ የፓርቲ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ጭምር እንደሚገኙበት ሜላተወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል።

ቦርዱ የሥነ-ምግባር ጉድለት የታየባቸውን አስፈጻሚዎች በማሰናበት በሌሎች እየተካ መሆኑንና የማጣራት ሥራውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።

በተጨማሪም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን ሂደት የሚታዘቡላቸውን ወኪሎች እንዲልኩ ጥሪ ተደርጎ ባጅ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ እስካሁን ወኪሎቻቸውን የላኩት ውስን ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸውን ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል።

ቦርዱ በምርጫው ሂደት የሚያጋጥሙ ማንኛቸውንም ችግሮች ለመፍታት ከቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ያሉ አሠራሮችን በመጠቀም ለምርጫው ስኬታማነት እንደሚሠራ አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...